Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ታይዋን በራሷ አቅም የተሰራ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይዋን በራሷ አቅም የተሰራ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች፡፡

ለታይዋን የመጀመሪያ የተባለው ይህ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ፕሬዚዳንት ሳዪ ኢንግዊን በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው፡፡

ባሕር ሰርጓጅ መርከቡ የታይዋንን የመከላከያ አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል፡፡

በተለይም ከቻይና በታይዋን ላይ ሊቃጣ የሚችልን ትንኮሳ ከመመከት አንጻር ባሕረ ሰርጓጅ መርከቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

የታይዋን ፕሬዚዳንት ሳዪ ኢንግዊን÷”የዛሬዋ ቀን በታይዋን ታሪክ ምን ጊዜም ስትወሳ ትኖራለች” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ባሕር ሰርጓጅ መርከብ በታይዋን አቅም መስራት እንደማይቻል ይታሰብ ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቷ÷ አሁን ግን ያን እሳቤ ውድቅ በማድረግ መስራት እንደምንችል አረጋግጠናል ብለዋል፡፡

1 ነጥብ 54 ቢሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት መርከቡ በኤሌክትሪክ እና ናፍታ እንደሚሰራ መገለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ባሕር ሰርጓጅ መርከቡ በርካታ ሙከራዎች ከተደረጉበት በኋላ በፈረንጆቹ 2024 ሥራ ላይ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version