አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቴሌኮም ሕብረት አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባኤውም “ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለዘላቂና ፍትሐዊ መጻኢ ጊዜ፤የአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራን ማፋጠን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በጉባኤው የኢኖቬሽንና ቴክኖልጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሶሎሞን ሶካ፣ የአፍሪካ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት፣ የልማት አጋር ድርጅቶች ተወካዮች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የሕብረቱ አህጉራዊ ጉባኤም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን÷ ከመስከረም 22 እስከ መስከረም 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚቆይ መገለጹን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
በጉባኤው የአፍሪካን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን እና ዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።