አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንዳዊው ቢሊየነር ሃርፓል ራንዳዋ እና የ22 ዓመት ወንድ ልጃቸው አሜር ካቤር በዚምባብዌ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ፡፡
የድርጅታቸው የአልማዝ ኩባንያ ሪዮዚም ንብረት የሆነው የግል አውሮፕላን ከሀራሬ ወደ ሙሮዋ ሲበር በዚምባቡዌ ደቡብ ምዕራብ ክልል የአልማዝ ማዕድን ማውጫ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የተከሰከሰው።
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች እና የበረራ አባላት በአደጋው ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
በአደጋው ሁለት የዚምባብዌ ዜጎች እና አራት የውጭ ዜጎች ህይወት ማለፉን ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል።
የድርጅቱ መስራች ራንድሃዋ በሪዮዚም ኩባንያ የ4 ቢሊዮን ዶላር ትልቅ አክሲዮን ድርሻ እንደነበራቸው በዘገባው ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!