Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በ100 ቀናት እቅድ አተገባበር ላይም እየተወያዬ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

መስተዳድር ምክር ቤቱ በክልሉ ሕጎች ሪፎርም ትግበራ እቅድ እንዲሁም በሌሎች ደንቦች ላይም ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version