አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የሪፐብሊካኑን አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲ ከሥልጣን አነሳ፡፡
ምክር ቤቱ ኬቨን ማካርቲን 216 ለ 210 በሆነ ያልተጠበቀ ድምፅ ከሥልጣናቸው ያነሳው በፓርቲያቸው ውስጥ በፈጠሩት አለመግባባት ነው ተብሏል፡፡
ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ምክንያት የሆነውን ድምፅ ከሰጡት መካከል ሥምንቱ ከራሳቸው ከሪፐብሊካኑ ወገን ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ ዴሞክራት መሆናቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ይሄው ትናንትና ምሽት ላይ የተሰጠው ድምጸ-ውሳኔ በሪፐብሊካኑ መካከል ብጥብጥ ማስነሳቱም ነው እየተነገረ ያለው፡፡
አሁን ላይ አፈ-ጉባዔውን የሚተካ ማን እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም፡፡
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ምክር ቤቱ በአስቸኳይ አዲስ አፈ-ጉባዔ እንደሚመርጥ ተሥፋ አደርጋለሁ ማለታቸውን የኋይት ሀውስ ፀሃፊ ካሪን ዣን ፒየር ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!