አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የሉክዘምበርግ አምባሳደር ጆርጅ ቴረስ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደር ምስጋኑ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎችን አብራርተዋል፡፡
ሉክዘምበርግ እስከፈረንጆቹ 2024 በተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነቷ ኢትዮጵያን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን እንደሚያጠናክሩ የገለጹት አምባሳደሩ፥ ሉክዘምበርግ በተለይም በፋይናንሱ ዘርፍ ያላትን ልምድ እንድታጋራም ጠይቀዋል።
አምባሳደር ጆርጅ ቴረስ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡