Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ኢሬቻ ሆረ-ፊንፊኔና አካባቢውን የማፅዳት መርሐ-ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት ኢሬቻ ሆረ-ፊንፊኔ እና አካባቢውን የማፅዳት መርሐ-ግብር ተካሄደ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ-ሲንቄዎች፣ ቄሮዎች፣ ቀሬዎቼ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች በተገኙበት የማክበሪያ ቦታውን የማፅዳት ስራው ተከናውኗል፡፡

አቶ ጥራቱ በየነ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ፥ የዛሬው የፅዳት መርሐ-ግብር ቦታውን ከማፅዳት ባለፈ የጋራ አብሮነታችንን የምናሳይበት ነው።

የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የአብሮነት፣ የተለያየ የሚገናኝበት፣ ከሁሉ በላይ ፈጣሪ የሚመሰገንበት በመሆኑ ሁላችንም ተቀራርበን አብሮነታችንን ከፍ እያደረግን አንድነታችንን እያፀናን ልናከብር ይገባል ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አቶ ጥራቱ አክለውም ፥ ኢትዮጵያ በርካታ እሴቶች ያላት ሀገር ስለሆነች ይህንን እሴት በአግባቡ ከተጠቀምን ለአንድነታችን ለእድገታችን ትልቅ አቅም ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።

#Ethiopia #Irreecha

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version