Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን በ114 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የንጹህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ሀርትሼክ ከተማ በ114 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ እና ከ50 ሺህ ባላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ የንጹህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአግልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

የክልሉ መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ሀርትሼክ ከተማ ያስመረቀው የውሀ ፕሮጀክት ሁለት ጥልቅ የውሃ ጉርጓድ ቁፋሮ፣ ማስፋፊያና የጥገና ስራዎችን ያካተተ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ነው ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡

ፕሮጀክቱ ከ50 ሺህ በላይ የህብረተሰበ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግና በአካባቢው የሚታየውን የንጹህ መጠጥ ውሀ እጥረት ለመፍታት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

እንዲሁም የክልሉ መንግስት ህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ የሚገኘውን ስራ እንደሚያሳይ መገለጹ የክልሉ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል፡፡

Exit mobile version