አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካና በአውስትራሊያ የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በክልሉ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች የ4 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡
ኑሯቸውን በአሜሪካ ቦስተን ያደረጉ ዳያስፖራዎች ከ3 ወራት በፊት በጅግጅጋ ከተማ ታይዋን የገበያ ማዕከል ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከ2 ሚሊየን 950 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
የገንዘብ ድጋፉን የአትላንቲክ ግሎባል ኤይድ ድርጅት ዳያስፖራዎችን በመወከል ለክልሉ አስረክቧል።
እንዲሁም በአውስትራሊያ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ያሰባሰቡትን የ1 ሚሊየን 86 ሺህ ብር ድጋፍ የዳያስፖራዎቹ ተወካይ እና የክልሉ የሀገር ሽማግሌ አቶ ሙሴ አብዱላሂ ለክልሉ አስረክበዋል።
በዚህ ወቅት የሥራ ሀላፊዎቹ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ተወላጆች በደረሰው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ነጋዴዎች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል፡፡