አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስደተኞች የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ዛሬ በሶስት ተቋማት መካከል ተፈርሟል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢፌዴሪ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽህፈት ቤት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ናቸው።
በስምምነቱ አማካኝነት ስደተኞች በዲጂታል መታወቂያው በኢትዮጵያ የሚሰጡ የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል።
ተቋማቱ የጋራ የመረጃ ልውውጥ እንደሚያደርጉና ስምምነቱም ኢትዮጵያ ለስደተኞች ያላትን በጎ አመለካከትና ተቀባይነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!