Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢሬቻ የእርቅ የአንድነት እና የሰላም በዓል ነው- ሃጂ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢሬቻ የልምላሜና ተስፋ አመላካች እንዲሁም የእርቅ ፣የሰላም እና የአብሮነት መገለጫ በዓል ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሃጂ አወል አርባ ተናገሩ።

የኢሬቻ በአል በክረምቱ ወራት ተራርቆ የከረመው ሕዝብ ዳግም ተገናኝቶና ተሰባስቦ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበትና አብሮነቱን የሚያጠናክርበት ነው ብለዋል፡፡

የተጣላና የተቀያየመ ተቀራርቦ በመነጋገር ሰላምና እርቅ ሳያወርድ በበአሉ ላይ መገኘትን የሚከለክለው የኢሬቻ በአል ያለፈ ቂምና ጥላቻ በፍቅር የሚታከምበት የይቅርታ በአል ነው ብሏል በመልእክታቸው።

የኢሬቻ በአል እንደ ሁልጊዜው የኦሮሞ ሕዝብ ባሕል ፣ ወግና መልካም እሴቶች ሁሉ በውበትና በድምቀት ጎልተው የሚታዩበት የሰላም ፣ የፍቅርና የደስታ በአል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version