Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከዘመን ዘመን፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን በሰላም ላሸጋገረው ፈጣሪ አምላኩን የሚያመሰግንበት እና የሚያከብርበት በዓል ነው ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ጸብን በይቅርታ የሚሻርበት፣ የሰላም፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ በዓል በመሆኑ መላው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ የተከበረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢሬቻ ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን ተራርቀው የቆዩ ዘመድ አዝማዶች የሚገናኙበት፣ አበቦች የሚፈኩበትና አዝርዕት የሚበቅልበት ወቅት የሚከበር በዓል መሆኑን ገልጸዋል።

ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ በደስታ፣ በፍቅር እና በአብሮነት ከሌሎች ወንድም እና እህት ብሔር ብሔረሰቦች ጋር የሚያከብረው የአደባባይ በዓል መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች በርካታ ባህልና ወግ ከኦሮሚያ ክልል ህዝብ ጋር የሚጋሩ በወንድማማችነት እና እህትማማችነት በጉርብትና በፍቅር የሚኖር በብዙ መልክአ ምድር የተሳሰረ ህዝብ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢሬቻ በዓል እሴት ጠብቀው ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፍ ያደረጉ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋልም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

በመጨረሻም፣ የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል እንዲሆን መመኘታቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version