አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ምሥራቅ ሕንድ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ56 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
በተጨማሪም 16 የሕንድ ወታደሮችን ጨምሮ ከ100 በላይ ዜጎች የገቡበት አልታወቀም ተብሏል፡፡
አደጋው የተከሰተው ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የሂማሊያ ባሕር ጠርዝ የበረዶ ግግሮች በመፈንዳታቸው ነው፡፡
አደጋውን ተከትሎም የ26 ሰዎች አስከሬን በሲኪም ግዛት አካባቢ እንዲሁም የ30 ሰዎች አስከሬን በቤንጋል ግዛት መገኘቱን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡
ከሟቾቹ መካከልም ሰባቱ የሕንድ ጦር አባላት መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
የጎርፍ አደጋው በሰዎች ላይ ካደረሰው ጉዳት በተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሙን የሕንድ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

