Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል 4 ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ክልል በሚገኙ አራት ወረዳዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ሎዋል ለኢዜአ እንደገለጹት የበረሃ አንበጣ መንጋው ከግንቦት 4/2012 ጀምሮ በመንጌሽ፣ጎደሬ፣ዲማና ጎግ ወረዳዎች ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋው በአሁኑ ወቅት በዛፎች ላይ የሰፈረ ሲሆን በምግብ ሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለም አስረድተዋል።

ህብረተሰቡ የተለያዩ ባህላዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የአንበጣ መንጋው ጉዳት እንዳያደርስ የመከላከል ስራውን እያከናወነ መሆኑን የገለጹት አቶ ኦጁሉ የክልሉ መንግስትም ባለሙያዎችን ማሰማራቱን አስረድተዋል ።

በአሁኑ ወቅት በፍጥነት እየተስፋፋ የሚገኘው የበረሃ አንበጣው በቀጣይ ጉዳት እንዳያደርስ ከባለሙያዎች ስምሪት ባለፈ ይሄንኑ የሚያስተባብር ግብረ-ሃይል እየተቋቋመ መሆኑንም ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version