Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋዛና ዌስት ባንክ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮሪደሮችን ለማስከፈት ስራ መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርድት የአለም ምግብ ፕሮግራም በጋዛ እና ዌስት ባንክ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮሪደሮችን ለማስከፈት ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የእርዳታ ኮሪደሩ ሲከፈት የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት በሚካሄድባቸው የጋዛ ሰርጥ እና ዌስት ባንክ አካባቢዎች የሚኖሩ 800 ሺህ ነዋሪዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተነግሯል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ የሚገባበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነፃ የሰብዓዊ ኮሪደሮች እንዲቋቋሙ እና የተቋሙ ሰራተኞችና የእርዳታ ቁሳቁሶች በነፃነት እንዲጓጓዙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዌስት ባንክ እና በጋዛ መካከል ያሉ ድንበሮች እና የፍተሻ ኬላዎች መዘጋታቸውን ገልጾ÷ በዚህም አስፈላጊውን ሰብዓዊ እርዳታ ለማስተላለፍ አለመቻሉን አመልክቷል፡፡

በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ሊከሰት የሚችለውን አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ ለመቋቋም በሚቀጥሉት አራት ሳምንታት ብቻ 17 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ማስታወቁን ሚድል ኢስት ሞኒተር አስነብቧል፡፡

Exit mobile version