Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቻይና አምባሳደር በእስራኤል በመኖሪያ ቤታቸው ውሥጥ ሞተው ተገኙ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 9፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና አምባሳደር በእስራኤል ዱ ዌይ በሰሜናዊ ቴል አቪቭ በሚገኘው አፓርታማቸው ውስጥ  ሞተው መገኘታቸውን አንድ የእስራኤል ባለስልጣን  ገለጹ፡፡

በአምባሳደሩ አሟሟት ዙሪያ የእስራኤል ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመው÷ በአሟሟታቸው ዙሪያ የተገኙት የመጀመሪያዎቹ ግኝቶች ምንም መጥፎ ሁኔታ አለመኖሩን እንደሚያሳዩም ነው ባለስልጣኑ የገለጹት ፡፡

አንድ የእስራኤል ፖሊስ ቃል አቀባይ በበኩላቸው÷ በመደበኛ አሰራር ሂደት የፖሊስ አባላት በቦታው ተገኝተው ምርመራ ጀምረዋል  ከማለት ውጪ  ተጨማሪ መረጃ አለመስጠታቸውም ነው የተነገረው።

ስማቸው ያልተጠቀሱ የሕክምና ምንጮችን በመጥቀስ የእስራኤል ቻናል 12 ቴሌቪዥን ጣቢያ አምባሳደር ሚን ዱ  በእንቅልፍ ወቅት በተፈጥሯዊ ምክንያቶች ሕይወታቸው ማለፉን ዘግቧልም ነው የተባለው፡፡

የ 57 ዓመቱ ሚስተር ዱ በየካቲት ውስጥ በእስራኤል የቻይና አምባሳደር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ከዚህ ቀደም የዩክሬን ልዑክ ሆነው ሲያገለግሉ  እንደነበርም ነው የተገለጸው፡፡

አምባሳደሩ ባለትዳርና ወንድ ልጅ የነበራቸው ቢሆንም ቤተሰባቸው በቅርቡ ወደ እስራኤል ሊጓዙ እንደነበረም ነው የተነገረው ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version