አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
የወረዳው ትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር ኃላፊ ዋና ሳጅን አማረ ታከለ እንደገለፁት፥ መነሻውን ሆሳዕና አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ኤፍ ኤስ አር (ታታ) መንገድ ስቶ በመውጣት መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ሆሳዕና ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ዶልፊን መኪና ላይ ጉዳት አድርሷል።
የአደጋው መንስዔ ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተነሳ እንደሆነ አስረድተው፤ በአደጋውም በ14 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰ ተናግረዋል።
አሽከርካሪዎች ተረጋግተው በማሽከርከር ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት እንዲታደጉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።
የሶዶ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ሰለሞን ሮባ በበኩላቸው፥ በአሁኑ ሰዓት ላይ እየተከሰተ ያለው የመኪና አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላክተዋል።
ከአዲስ አበባ እስከ ቡታጀራ ድረስ ያለው መንገድ በመበላሸቱ ምክንያት የትራፊክ አደጋ እየከፋ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ዛሬ አደጋ በደረሰበት ስፍራ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከባድ የመኪና አደጋ መድረሱን አስታውሰዋል።
ችግሩን በጊዜያዊነት ለማቃለል የፍጥነት መቆጣጠሪያ እንሰራለን ማለታቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!