አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እፀገነት በዛብህ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለብሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫራይስት ንዳዪሺሚዬ አቅርበዋል።
በዚህ ወቅት አምባሳደር እፀገነት ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ለፕሬዚዳንቱ እንዲሁም ለቡሩንዲ ህዝብ የተላከን የሰላምታ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አምባሳደሯ ፥ በቀጣይ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ከብሩንዲ መንግስት እና ህዝብ ጋር በቅርበት ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡