Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የልብ ሕክምና አገልግሎትን በተለያዩ አካባቢዎች የማስፋት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው – ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የልብ ሕክምና አገልግሎትን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች የማስፋት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።

የዓለም የልብ ቀን “ስለልብዎ ይወቁ ልብዎን ይንከባከቡ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ተከብሯል።በመርሐ ግብሩ ላይ ዶክተር ሊያ ታደሰ ÷ በኢትዮጵያ የልብ ህክምና ፈላጊዎች ቁጥር እየተሰጠ ካለው አገልግሎት አንፃር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የልብ ህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችሉ ስራዎች መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።

ከአዲስ አበባ በተጨማሪ የልብ ህክምና አገልግሎትን በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች የማስፋት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

የኢትዮጵያ የልብ ማህበር ፕሬዚዳንት እንዳለ ገብሬ በበኩላቸው ÷ የዓለም ስጋት የሆነውን የልብ በሽታ ለማከም ቅንጅታዊ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት ህክምናውን ለማስፋት የሚያደርገውን ጥረት የግሉ ዘርፍም አጋዥ በመሆን ለስኬቱ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

በመርሐ ግብሩ የልብ ህሙማን ማህበርና የኢትዮ ኢስታቡል ጀነራል ሆስፒታል ለ300 ሕጻናት ነጻ የልብ ቆዶ ህክምና ለመሥጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

Exit mobile version