Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን-ኮሚሸነር ደመላሽ ገብረሚካኤል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሉዓላዊነትና የነፃነታችን ዓርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን ሲሉ የኢትዮጵያ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሸነር ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ።

16ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን እና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ሃሳብ በፌዴራል ፖሊስ ቅጥር ግቢ ተከብሯል።

በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና አባላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ጊዜ፥አባቶቻችን ያስረከቡንን የሉዓላዊነት ምልክት፣ የነፃነታችን ዓርማ እና የክብራችን መገለጫ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን የህይወት መስዕዋትነት በመክፈል ጭምር እንጠብቀዋለን ብለዋል።

በመላው ሀገሪቱ ያሉ የፖሊስ አባላት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ዘወትር ዘብ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

በዓሉ በፓናል ውይይትና ሌሎች የሰንደቅ ዓላማን ክብር ከፍ በሚያደርጉ ዝግጅቶች በመከበር ላይ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version