Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግና ፓርቲ የሚጋጥሙትን ተግዳሮቶች በሀገር በቀል እሳቤዎች እየፈታ ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ያደርጋል- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የሚጋጥሙትን ተግዳሮቶች በሀገር በቀል እሳቤዎች እየፈታ ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ያደርጋል ሲሉ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በሐዋሳ የስልጠና ማዕከል ለፓርቲው አመራር አባላት እየተሰጠ ያለውን የስልጠና ሒደት ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ጊዜ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት÷በሀገሪቱ የተለያዩ ማዕከላት እየተሰጠ ያለው ስልጠና በታቀደው መሰረት በስኬታማነት እየተካሄደ ነው፡፡

ስልጠናው ፓርቲው በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከህዝብ የተቀበለውን አደራ በውጤታማነት እንዲወጣ የሚያግዘው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአመራር አባላቱ ከዚህ ቀደም በተገኙ ስኬቶች የጋራ መግባባት የሚፈጥርበትና በጉድለቶቹም የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያመላክትበት መድረክ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡

የስልጠናው ዓላማ ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግና በሀገር በቀል እሳቤዎች ሀገርን ማበልጸግ እንደሚቻል ማረጋገጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአመራር አባላቱ በየአካባቢው የብልጽግናን እሳቤ መሬት ለማውረድ የሚደረጉ ጥረቶችን በመመልከት ልምድ የሚለዋወጥበትን የስልጠና አካሄድ መከተላቸውንም ተናግረዋል፡፡

በስልጠናው የሚቀርቡ ርዕሰ ጉዳዮች ወቅቱን የዋጁና የአመራር አባላቱን አቅም የሚያጎለብቱ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ በአንዳንድ አካባቢዎች ውጤታማ ስራ ተከናውኗልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሰልጣኞቹ ወደ ሕዝቡ ሲወርዱ ያገኙትን እውቀት እና ልምድ ተጠቅመው በተግባር እንዲያረጋግጡም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Exit mobile version