አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭትን ለማርገብ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እና ቅንጅት በማደስ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።
በመካከለኛው ምስራቅ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ዛይ ጁን ከሩሲያ የመካከለኛው ምስራቅ እና የአፍሪካ ሀገራት ልዩ ተወካይ ጋር በትናንትናው ዕለት በኳታር ዶሃ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ቻይና እና ሩሲያ በፍልስጤም ጉዳይ ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው መናገራቸው ተጠቅሷል።
“አሁን ላይ በፍልስጤም እና እስራኤል ግጭት ውስጥ ያለው መሰረታዊ ምክንያት የፍልስጤም ህዝብ ህጋዊ መብቶች አለመረጋገጥ ነው” ሲሉም ዛይ ተናግረዋል።
ቻይና የግጭቱ ሰለባ ለሆኑ ንፁሃን እና በደረሰው ሰብአዊ ቀውስ እንዳዘነች መግለፃቸውን ሰንደይ ታይምስ ዘግቧል፡፡
ሀገራቸው የፍልስጤም እና የእስራኤል የሰላም ድርድር እንደገና እንዲጀመር እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት መፍትሄ በትክክለኛ መንገድ እንዲተገበር አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።
ባለፈው ቅዳሜ ከአረብ ሊግ ተወካዮች እና በቻይና የእስራኤል አምባሳደር ጋር የተገናኙት ዛይ፥ ቻይና በፍልስጤም ጉዳይ ላይ “የራስ ወዳድ” ፍላጎት እንደሌላት አስረድተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!