Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል መመሪያ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 10 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ከስደት ተመላሾችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል መመሪያ ላይ በቢሾፍቱ ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ÷ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን የመከላከልና ከስደት ተመላሾችን መልሶ የማቋቋም ሀላፊነት አለብን ነው ያሉት።

“ለዜጎች ከፍተኛ የሥራ እድል እየፈጠርን ያለነው በሀገር ውስጥ ስራዎች ላይ ነው” ያሉት አቶ ንጉሱ “ከዚህ አልፎም ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ወደውጭ ሀገር ለሥራ እናሰማራለን” ብለዋል።

ይህንን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ግን ሥርአት ባለውና በህጋዊ መንገድ መምራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች በጉዳዩ ላይ ከሚሰሩ ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን አካላዊና አዕምሯዊ ጉዳት ደርሶባቸው ወደሀገር የሚመለሱ ዜጎችን ችግር ፈትቶ በዘላቂነት ወደሥራ ለማሰማራት እንደሚሰራም ነው የተናገሩት።

ሚኒስቴር ዴኤታው ተጎጂ ከስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋምና አሰልጥኖ ወደሥራ ለማሰማራት የምንመራበትን መመሪያ እንፈትሻለንም ብለዋል በንግግራቸው።

በታምሩ ከፈለኝ

 

 

 

Exit mobile version