Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች በጋዛ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች በጋዛ ሰርጥ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኤጀንሲዎቹ ጥሪውን ያቀረቡት በጋዛ ሰርጥ የሚስተዋለው የሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትና የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ አምስት የተመድ  የሰብዓዊ እርዳታ ኤጀንሲዎች እንዳስታወቁት÷አሁን ላይ በጋዛ  ሰርጥ ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊ ነው፡፡

ስለሆነም በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ  ነው ኤጀንሲዎቹ ጥሪ ያቀረቡት፡፡

ከዚህ ባለፈም በጋዛ እናቶችና ሕጻናትን ጨምሮ ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የእስራሴል እና ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በትናንትናው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ 20 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ ገብተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ድጋፉ አሁን ላይ በጋዛ ከሚያስፈለገው የሰብዓዊ እርዳታ አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊትም በጋዛ የሚኖሩ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች ሕይወታቸው በእርዳታ ላይ ጥገኛ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ሃማስ ከሁለት ሳምንት በፊት በእስራኤል ላይ በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት እስካሁን 1 ሺህ 400 እስራኤላውያን ለሕልፈት መዳረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ እስራኤል በሃማሳ ላይ እየወሰደች ባለው አጸፋዊ እርምጃ እስካሁን በጋዛ ከ4 ሺህ 300 በላይ ዜጎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

Exit mobile version