አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚዳንት ሳዳም ሁሴን ሴት ልጅ ራጋድ ሳዳም ሁሴን በህግ እንዲፈርስ የተደረገውንና አባቷ ይመሩት የነበረውን ባዝ ፓርቲ በማስተዋወቋ የሠባት ዓመት እስራት በባግዳድ ፍርድ ቤት ተፈርዶባታል፡፡
በፈረንጆቹ 2003 አሜሪካ ኢራቅን በወረረችበት ወቅት ሣዳም ሁሴን ከስልጣን ሲወገዱ ፓርቲያቸውም እንዲታገድና እንዲፈርስ ተደርጎ ነበር።
በዚህም ራጋድ ሁሴን በፈረንጆቹ 2021 በቴሌቪዥን ቃለ-መጠይቆች ላይ የባዝ ፓርቲን እንቅስቃሴ በማስተዋወቅ ጥፋተኛ ሆና ተገኝታለች ነው የተባለው፡፡
በዚህም በሌለችበት የሠባት ዓመት እስራት ፍርድ ተላልፎባታል ተብሏል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በዮርዳኖስ ከእህቷ ራና ጋር የምትኖረው ራጋድ መቀመጫውን ሳዑዲ ካደረገው የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ፥ ኢራን በኢራቅ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ጠንካራ አቋም ወስዳለች ሲልም ነው ዘ ዊክ በዘገባው ያመላከተው፡፡
ወንድሞቿ ኡዴይ እና ቁሴይ በ2003 በሞሱል በአሜሪካ እንደተገደሉ መረጃው አስታውሷል፡፡ በሳዳም ሁሴን የኢራቅ አገዛዝ ጭቆና፣ ስደት፣ ሁከትና ብጥብጥ በዜጎቹ ዘንድ የሚታወስ እንደሆነም ነው መረጃው የሚያነሳው፡፡
ሆኖም የሳዳም ሁሴን ልጅ ራጋድ ብዙ ሰዎች አባቷ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ኢራቅ ሀብታም፣ የተረጋጋች እንደነበረች ይነግሩኛል ያለች ሲሆን ፥ ጊዜውም የደስታና የኩራት እንደነበር አጫውተውኛል ብላለች ለአል አረብያ በሰጠችው ቃለ-ምልልስ፡፡
በፈረንጆቹ 2018 የኢራቅ ባለስልጣናት የአይኤስአይኤስ፣ አልቃይዳ እና ሌሎች የባዝ ፓርቲ አባል ከሆኑ ሰዎች ጋር በሀገሪቱ በወንጀል የሚፈለጉ ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋት እንደነበር ይታወሳል፡፡
#Iraq
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!