አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሸን ለሀገራዊ የምክክር አጀንዳ የሚለዩትን በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ማስመረጥ ጀምሯል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብሌን ገብረ መድኅን በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ ሀገራዊ ምክክር የተለያየ ቋንቋ፣ ሐይማኖት እና ባሕል ያላቸው ሰዎች ሁሉን አካታች በሆነ የአሠራር ሥርዓት ላለመግባባት ምክንያት በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚመካከሩበትና ወደ መግባባት የሚሸጋገሩበት ሂደት ነው፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ለሀገር ሰላምና ዘላቂ አብሮነት የሚነሱ ሐሳቦችን ተሳታፊዎች ለሕብረተሰቡ ማስረዳት እንሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡
በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ከአራት ወረዳዎች የተውጣጡ 400 ሰዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት ከማንዱራ፣ፓዊና ዳንጉር ወረዳዎች እና ከግልገል በለስ ከተማ የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በነገው ዕለት ደግሞ የጉባ፣ ወምበራ፣ ቡለንና ድባጢ ወረዳ ተሳታፊዎች መድረክ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!