Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተመድ በሊባኖስና እስራኤል ድንበር ላይ ያለው የእርስ በርስ ውጥረት እንዲሻሻል አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ልዩ አስተባባሪ ጆአና ሮኔካ በሊባኖስ እና በእስራኤል ድንበር ላይ ያለው የእርስ በርስ ውጥረት እንዲሻሻል አሳስበዋል፡፡

ተመድ ሊባኖስ በአስቸጋሪ ወቅት ደህንነቷን እና መረጋጋቷን ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ያልተቋረጠ ድጋፍ መስፋቱን ገልጸዋል፡፡

“በተመድ ቻርተር ላይ የተደነገገው 193ቱ የድርጅቱ ዋና ዓላማ ተተኪ ትውልድን ከጦርነት መቅሰፍት መታደግ ነው” ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

የሰላም እና የፀጥታ አደጋዎች በሊባኖስ እና በአከባቢው እየጨመሩ መጥተዋል ያሉት ልዩ አስተባባሪዋ፥ ለሰላም እና ለሊባኖስ ህዝቦች ቀጣይ ደህንነት ላይ መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

አክለውም፥ በሊባኖስ እና እስራኤል ድንበር ላይ የሚካሄደው ተኩስ ከፍተኛ ስጋት እንደጋረጠ በመግለጽ በአካባቢው የሚካሄደው ሁከት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ጦርነቱ እንዲቆም እና የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1701 ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረግም ነው የጠየቁት፡፡

በሊባኖስ የተመድ ጊዜያዊ ሃይል የተልእኮ መሪ እና የሃይል አዛዥ አሮልዶ ላዛሮ እንደተናገሩት፥ የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከሊባኖስ ጦር ሃይሎች ጋር በመሆን በደቡባዊ ሊባኖስ አካባቢ ቅኝት ማድረጋቸውንም ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ውጥረቱን ለማርገብ እና አለመግባባቶችን ለማስወገድ ጥረት መደረጉን እንደገለጹ ዢንዋ ዘግቧል።

የሊባኖስ እና የእስራኤል ድንበር ሃማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ለመደገፍ በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ላይ ሂዝቦላ በደርዘን የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ ሼባ እርሻዎች ከተኮሰ በኋላ የሊባኖስና የእስራኤል ድንበር ውጥረቱ ጨምሯል።

ይሕም የእስራኤል ጦር ወደ ደቡብ ምስራቅ ሊባኖስ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ምላሽ እንዲሰጥ ማድረጉም ነው የተሰማው፡፡

#UN #lebanon #Israel #Palestine

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version