Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አመራሩ የጠራና የጋራ አቋም ይዞ ለዘላቂ ሰላምና ልማት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየደረጃው ያለው አመራር የጠራና የጋራ አቋም ይዞ ለዘላቂ ሰላምና ልማት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴን አስገነዘቡ፡፡

በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታዎችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎ፣ የዋግኽምራ፣ ደሴ፣ ወልድያና ኮምቦልቻ ከተሞች አስተዳደር አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለህዝብ የሚያስብ ማንኛውም አካል ለውይይትና ለንግግር መዘጋጀት እንዳለበት ጠቅሰው፤ ከሰላም እጦት በፍጥነት በመውጣት የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የልማት ጥያቄዎችን መመለስ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለዚህም በመጀመሪያ አመራሩ ግልጽና የጠራ መረጃ፣ ወኔና ብርታት ሊኖረው ይገባል ማለታቸውን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

በህግ ማስከበር ስራው የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል መረባረብ እንደሚገባ አመልክተው፤ እያንዳንዱ ቀበሌ፣ ወረዳና ዞን የአካባቢውን ሰላም በራሱ ማስጠበቅ እንዲችል እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳድር ዞንና የደብረ ብርሀን አመራሮች በደብረ ብርሀን ከተማ ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው÷ውይይቱ የክልሉን የመልማትና የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችል አቅም ይፈጠራል ብለዋል፡፡

በአላዩ ገረመውና

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version