Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መቄዶኒያ የ27 ሚሊየን ብር ቤት ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓልም ሪል ስቴት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለመቄዶኒያ የአዕምሮ ህሙማን መርጃ የ27 ሚሊየን ብር ቤት ድጋፍ አደረገ።
ተቋሙ በገርጂ መብራት ሀይል ሳይት ካሉ አፓርትመንት ቤቶች አንድ ባለ 177 ካሬ ሜትር ባለ ሶስት መኝታ ድጋፍ ማድረጉ ነው የተገለፀው።
የፓልም ሪል ስቴት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰላማዊት አያሌው፥ “ተቋማችን ከሪል ስቴት ልማት ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት በማለም ስጦታውን ለማድረግ ወስኗል” ብለዋል።
የመቄዶኒያ መስራች አቶ ቢንያም በበኩላቸው የፓልም ሪል ስቴት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሌሎች በሪል ስቴትና መሰል ዘርፎች የተሰማሩ አካላት የፓልም ሪል ስቴትን ፈለግ በመከተል ማዕከሉን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ማዕከሉ ከ7 ሺህ 500 በላይ የአዕምሮ ህሙማንንና አረጋውያንን በ25 ከተሞች በሚገኙ ማዕከላቱ ተረጂዎችን የመንከባብ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን አሁንም ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገልጿል።
በታሪኩ ወልደሰንበት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version