Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ80 እስከ 90 በመቶ ያህሉ የሳይበር ጥቃት በተጠቃሚዎቹ ግንዛቤ ማነስ እንደሚከሰት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳይበር ደኅንነት ላይ ከሚደርሱ ጥቃቶች ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው በተጠቃሚዎቹ የግንዛቤ ማነስ የሚከሰት መሆኑ ተገለጸ፡፡

3ኛ ሣምንቱን የያዘው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር በመከበር ላይ ይገኛል፡፡

በአከባበሩ ላይ እንደተገለጸው÷ እየጨመረ የመጣውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የተጠቃሚዎችን ንቃተ- ኅሊና ማሣደግ ይገባል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሳይበር አጠቃቀም ላይ ያለውን የግንዛቤ ደረጃ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት በአከባበሩ ላይ ይፋ ተደርጓል።

በትዕግስት ብርሃን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version