Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሠሪ፣ ሠራተኛ እና መንግሥት አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ላይ ÷ የሥራና ክኅሎት ሚንስቴር፣ ጤና ሚንስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የሁለቱ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አማካሪ ቦርድ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር እና የአማካሪ ቦርዱ ሰብሳቢ ሙፈሪሃት ካሚል÷ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ በሚኒስቴሩ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል፡፡

ዘርፉን አንዱ ጨቋኝ ሌላው ተጨቋኝ ከሚሆኑበት አስተሳበሰብ በማላቀቅ ሁለቱንም እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሠራተኛውን አካላዊ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የሥራ አካባቢ ደኅንነቱ የተረጋገጠ፣ እጅና አዕምሮው የተፍታታ እና በቂ ክኅሎት የታጠቀ በማድረግ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻልም ነው ያመላከቱት፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ ቦርዱ እንዲጠናከር በማድረግ እና ከአሠሪና ሠራተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በጋራ በትኩረት ለመፍታት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

የአማካሪ ቦርዱ ረቂቅ ዕቅድ በመድረኩ ላይ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትም ተገልጿል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version