Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ም/ቤት ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት የውጭ አማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙን ገለጸ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀድሞ ዳኞች፣ ልምድ እና ብቃት ካላቸው የሕግ ባለሙያዎች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ከተውጣጡ አካላት የአማካሪ ምክር ቤት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በተገኙበት ማቋቋሙ ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 53 ስር የተመለከተውን የሕግ ድንጋጌ መነሻ በማድረግ በወጣው መመሪያ ቁጥር 16/205 መሠረት የተቋቋመ ነው ተብሏል፡፡

ምክር ቤቱን ማቋቋም ያስፈለገበት ዋና ዓላማ የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል የሚረዱ አስገዳጅ ያልሆኑ ምክረ ሀሳቦችን በማመንጨት እና አስተያየት በማቅረብ የዳኝነት ስርዓቱን ለማሻሻል እና ለማዘመን በሚሰሩ ሁለንተናዊ የለውጥ ስራዎች ላይ ሙያዊ እገዛ እንዲያደርጉ ለማስቻል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ምክር ቤቱ ዘጠኝ አባላት እንዳሉት የተገለጸ ሲሆን አቶ እስራኤል ተክሌ በሰብሳቢነት እንዲሁም ሙራዶ አብዶ (ዶ/ር) በምክትል ሰብሳቢነት መመደባቸውን የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክር ቤቱ ተጠሪነቱ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሲሆን፥ ዳኛ አበበ ሰለሞን ከፍርድ ቤቱ በኩል የምክር ቤቱ ጸሐፊ በመሆን በፕሬዚዳንቱ ተመድበዋል፡፡

Exit mobile version