አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ኅብረ- ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓቱ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ያለውን ሚና በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባዔ ዛህራ ሁመድ ገለፁ።
በዓሉን ሕገ- መንግሥቱንና ኅብረ- ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓቱ አስተምኅሮን በአግባቡ ተደራሽ ባደረገ መልኩ በስኬት ለማክበር የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልል እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ምክትል አፈ- ጉባዔዎች እየተሳተፉ ነው፡፡
በዓሉ ቀኑን ከማሰብ ባለፈ ሕገ- መንግሥታዊ ቃል ኪዳን የሚታደስበት እና ኅብረ- ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓቱ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳለው በማረጋገጥ እንደሚከበር ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ ገልጸዋል፡፡
ኅብረ- ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓቱ ለሕዝቦች እኩልነት፣ ነፃነትና አንድነት ዋስትና የሰጠ መሆኑን አስታውሰው÷ በዓሉ ብዝኃነት፣ መቻቻል እና አብሮነትን በማጎልበት ዴሞክራሲና ዘላቂ ሰላምን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል።
በዓሉ የብሔር ብሔረሰቦችን ባሕልና ዕሴቶች ለማጎልበት ፋይዳ አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በዓሉ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እርስ በራሳቸው ከመተዋወቅ ባለፈ ትስስራቸውን የሚያጠናክሩበት በመሆኑ ሀገራዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጎልበት የጎላ ሚና እንዳለው ተመላክቷል፡፡
18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በመጪው ሕዳር 29 ቀን 2016 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ይከበራል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!