አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ለሶማሌ ክልል ሦስት የውሃ ቦቴዎችን በድጋፍ አበርክቷል።
ድጋፉን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በጅግጅጋ ከተማ ተገኝተው ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስረክበዋል፡፡
አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ሚኒስቴሩ ለክልሉ ሕዝብ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው፤ የውሃ ቦቴዎቹ በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ንጽሕና አጠባበቅና በተደጋጋሚ በክልሉ ቆላማ አከባቢዎች የሚከሰተውን ድርቅና የውሃ እጥረት ለማቋቋም እንደሚውሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለሌሎች በክልሉ እየተከናወኑ ላሉ የመሰረተ ልማት ሥራዎች እንደሚውሉ መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡