Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኮሚሽኑ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር የሥራ ትውውቅ መድረክ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ጋር የሥራ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚሠራቸውን ተግባራት አስመልከቶ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡

ኮሚሽኑ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከጥቅምት 22 እስከ 24 ባሉት ቀናት ከክልሉ ለተውጣጡ ተባባሪ አካላት በሆሳዕና ከተማ ሥልጠና እንደሚሰጥ መገለጹንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ የሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)፣ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክልትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

Exit mobile version