አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) በመተከል ዞን ባለፉት ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የትምሕርት ተቋማት መልሶ በመገንባት የትሕምርት ተደራሽነትን ለማስፋት ሕብረተሰቡ እንዲረባረብ ጥሪ ቀረበ፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ የተመራ ልዑክ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ፎቶ ማንጃሪ 1ኛ ደረጃ ትምሕርት ቤትን ጎብኝቷል፡፡
አቶ ጌታሁን በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ተማሪዎች መደበኛ ትምሕርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በክልሉ ትምሕርት ቢሮ አማካኝነት ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሶች ድጋፍ መደረጉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ባለፉት ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የትምሕርት ተቋማት መልሶ በመገንባት የትሕምርት ተደራሽነትን ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ሕብረተሰቡ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!