አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምክር ቤት አባላት መጪው ዘመን የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ዕውቀት ማጎልበት እንደሚጠበቅባቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ሎሚ በዶ አስገነዘቡ፡፡
በአፍሪካ አመራር ልኅቀት አካዳሚ ለምክር ቤት አባላት እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በዛሬው ውሎም “ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያና ተያያዥ ዕድሎች” በሚል መሪ ሐሳብ በዲጅታል አመራር፣ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት እና እየመጣ ያለው ዓለም አቀፍ ለውጥ ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ ወ/ሮ ለሚ በዶ እንደገለጹት÷ በምክር ቤት ሥራዎች በተለይም አባላቱ ለሚያደርጓቸው የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች ቴክኖሎጂ አጋዥ ስለሆነ አጠቃቀምን ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትሩ አብረሀም በላይ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት በአግባቡ እና በዕውቀት ከተመራ በአጭር ጊዜ ሀገርን ማሣደግ ያስችላል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያም በመስኩ ትልቅ ተቋም እና የመረጃ ማዕከል ገንብታ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ትላልቅ ተግባራትን እየፈፀመች ትገኛለች ማለታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!