አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የቱሪዝም ልማትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ በተመለከተ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለፃ አድርጓል።
ለአምባሳደሮቹና ዲፕሎማቶቹ ማብራሪያ የሰጡት የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ÷ የቱሪዝም ሀብትና የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅና ዘርፉን በማዘመን በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቱሪዝም ሀብታቸው ቀዳሚ ከሚባሉ ሀገራት መካከል የምትጠቀስ ቢሆንም ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በአግባቡ ሳታገኝ መቆየቷን ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ነባሮቹን የቱሪስት መዳረሻዎች ይበልጥ ዘመናዊና ሳቢ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ነው ያሉት።
በአዲስ አበባ በአጭር ግዜ ተገንብተው የተጠናቀቁት ገበታ ለሸገርና የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ለቱሪስቶች ምቹ ሁኔታን የፈጠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በመሆኑም ጥንታዊ ቅርሶችና አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ለቱሪስቶች ምቹ በመሆናቸው ሁሉም እንዲጎበኝ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከገለፃው በኋላም ዲፕሎማቶቹ በሳይንስ ሙዝየም የተዘጋጀውን የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ አውደ ርእይ መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!