Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ከ80 ሚሊየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይጠበቃል

 

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2015/2016 የመኸር ወቅት ከለማ የስንዴ ሰብል ከ80 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በክላስተር የለማ የመኸር ስንዴ ምርት የመሰብሰብ ዘመቻን አስጀምሯል፡፡

ምርት የመሰብሰብ ዘመቻው የተጀመረው በክልሉ ምዕራብ አርሲ ዞን ገዳብ ሃሳሳ ወረዳ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ በ2015/2016 የመኸር ወቅት ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ ስንዴ መልማቱ ተመላክቷል፡፡

ከዚህም 80 ሚሊየን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version