Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ በአፍሪካ የማዕድን ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በአፍሪካ የማዕድን ዘርፍ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ጥሪ ቀረበ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ የሚካሄደው የአፍሪካ-አሜሪካ የንግድ ጉባዔ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ፥የአሜሪካ ኢንቨስትመንት የአፍሪካ ሀገራት ማዕድናትን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ኢኮኖሚያቸውን በኢንዱስትሪ እንዲያሳድጉ ይረዳል ብለዋል፡፡

አፍሪካ ወሳኝ የጥሬ ዕቃ ምንጭ ናት ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፥ ሆኖም ግን የሸቀጥ አምራች ብቻ መባልን አንሻም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በመዋዕለ ንዋይ የሚመራ አቀራረብን በማዘጋጀት ዓለም አቀፍ ወሳኝ የማዕድን አቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማስፋት እንድትሰራ ጥረት እንደሚደረግም አንስተዋል።

የአፍሪካ ምድር የተፈጥሮ ሃብት በብዛት የሚገኝባት አህጉር መሆኗን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ ፥ 40 በመቶ የሚሆነው የዓለም ወርቅ የሚገኝባትና እና የኮባልት፣ ዩራኒየም፣ ፕላቲኒየም እና አልማዝ ክምችት ባለቤት ናት ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት አሁንም ከፍተኛ የሆነ ድህነት ውስጥ እንደሚገኙ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

ጉባዔ በአፍሪካ እና አሜሪካ መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በፈረንጆቹ 2000 የተላለፈውን የአፍሪካ የእድገት እና እድል ድንጋጌ (አጎዋ) አስመልክቶ የሚካሄድ እንደሆነ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የአፍሪ ሀገራት ከቀረጥ ነጻ ጥሬ እቃዎችን ለአሜሪካ ገበያ የሚቀርቡበት የአፍሪካ የእድገትና እድል ድንጋጌ (አጎዋ) ፥ በፈረንጆቹ መስከረም 2025 ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

በዚህም የአፍሪካ ሀገራት የንግድ ድርጅቶችን እና ባለሃብቶችን ለማረጋጋት ምንም አይነት ለውጥ ሳይደረግ ለ10 ዓመት እንዲራዘም ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በጉባዔው ላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፥ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር አጎዋን ያለምንም ለውጥ እንዲራዘም ማድረግ ብቻ ሣይሆን ለማሻሻል ከኮንግረሱ ጋር መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

#Africa #Ethiopia #America #AGOA

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version