አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በ8ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 690 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አስመርቋል።
በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም ፥ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በሰላም ዘርፍ የሚያደርጉት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ።
የሰላም መልዕክተኞቹ በሚሰማሩባቸው ክልሎች የሀገር በቀል ዕሴቶችን እንዲገበዩና ህብረተሰቡን በቅንነት እንዲያገለግሉም አሳስበዋል፡፡
የበጎ ፍቃድ ተግባር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማሳደግ የሚቻልበት የፍቅር ተግባር ነው ሲሉም አውስተዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ታደሰ ሀብታሙ(ዶ/ር) በበኩላቸው ፥ ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጣኞችን በመቀበልና በማሰልጠን ለበጎ ሥራና ለሰላም ግንባታ አጋር መሆን ችለናል ብለዋል፡፡
‘‘በማኅበረሰብ ውስጥ ነን’’ የሚለውን የጅማ ዩኒቨርሲቲ መሪ ቃል በተግባር ያሳየንበት ብሎም የሰላም አምባሳደር መሆናችንን ያስመሰከርንበት ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በሀገሪቱ በሥምንት ዙር ከ 46 ሺህ 600 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሰልጣኞች ማሰልጠን መቻሉ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
በተስፋሁን ከበደ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!