Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ ከ779 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እያገኙ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ከ779 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምገባ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የምገባ አገልግሎቱን እያገኙ የሚገኙት በ779 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው፡፡

ተማሪዎች በምግብና በግብዓት አቅርቦት ችግር ሳቢያ ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ በኃላፊነት እየተሠራ መሆኑን የኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ ስንታየሁ ማሞ ተናግረዋል፡፡

የምገባ አገልግሎቱ በ2013 ዓ.ም ሲጀመር የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ቁጥር 350 ሺህ እንደነበር አስታውሰው ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡

ከተማሪዎች የምገባ አገልግሎት በተጨማሪ የተማሪዎች ደንብ ልብስ (ዩኒፎርም)፣ ደብተርና የመማሪያ ቁሶች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በምገባ መርሐ-ግብሩ ለ16 ሺህ መጋቢ እናቶች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version