አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይቅ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሚሠጠውን ግዳጅ መፈፀም በሚያስችለው ቁመና ላይ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል ሲሉ ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሠጥአርጌ ገለጹ፡፡
በቀጣናው ሕገ-ወጥ ቡድኖችን ለማፅዳት ሠራዊቱ በሚያከናውነው ተልዕኮ የከተማዋ የፖሊስ አባላትና ሚሊሻ በቁርጠኝነት በመሠለፍ በተካሄደው ኦፕሬሽን ሕገ- ወጥ ቡድኑ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ደርሷል ብለዋል ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ፡፡
ሠራዊቱ ከሐይቅ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመተባበር በሕገ-ወጥ ቡድኑ እጅ የነበሩ የጦር መሣሪያዎችን ይዟል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሕገ- ወጥ ቡድኑን አባላት ከማሕበረሰቡ ነጥሎ ለማውጣት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።