አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር 139 ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መመለሱን አስታወቀ።
ተመላሾቹ በዚህ ሣምንት በሁለት ዙር በተደረገ ትብብር ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆናቸውን በጁቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
የኢትዮ-ጂቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛና የተለያዩ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች በተደራጀ መልኩ የሚፈፀምበት ቦታ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ዜጎችን ለሞት እየዳረገ ያለ አስፈሪ መንገድ ነው ተብሏል።
ይህንን ለመቅረፍም በሚዲያ ተቋማት ማህበረሰቡን በማስተማር፣ ከህግ እና ጸጥታ ተቋማት ጋር ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ በጋራ በመስራት እንዲሁም ፍልሰተኞችን ወደ ሀገር ቤት በመላክ በየቀኑ እየተባባሰ ያለውን የስደት ሞት መቀነስ ያስፈልጋል ነው የተባለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!