Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተመድ በጋዛ እና በዩክሬን የተኩስ አቁም ማስፈን ያልቻለ ‘ፋይዳ የሌለው ድርጅት’ ሆኗል- ጄፍሪ ሮበርትሰን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ እና በዩክሬን የተኩስ አቁም ማስፈን ያልቻለ ‘ፋይዳ የሌለው ድርጅት’ ሆኗል ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ጄፍሪ ሮበርትሰን ተናግረዋል።
ከአልጀዚራ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ “ፑቲን እና ኔታንያሁ በፈጸሙት የጦር ወንጀል መካከል ምንም ልዩነት የለም” ብለዋል።
“ሁለቱም ያለ ልዩነት ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ ነው የተባበሩት መንግስታት ግን አሁንም ለውጥ ማምጣት ያልቻለ ፋይዳ የሌለው ተቋም ነው” ሲሉም አክለዋል።
አያይዘውም “ተመድ ለቆመለት ዓላማ ብቁ አይደለም ምክንያቱም የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ነገሮችን ከመተግበር ይልቅ ማውራት የሚቀለው ፋይዳ ቢስ ተቋም ነው” ሲሉም ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።
“ሌላው ቀርቶ ምክር ቤቱ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ለመድረስ የቀረበው ሃሳብ ሩሲያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብረቷን ተጠቅማ ውድቅ ሲደረግበት ያለው ስልጣን ያላገዘው” ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡
ባለፈው ሳምንትም ከጋዛ ጋር በተያያዘ የቀረበው የተኩስ አቁም ውሳኔ በአሜሪካ ውድቅ መደረጉን አንስተዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በ78ኛው የተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ድርጅቱ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን የተሻሻለ፣ ብቁ እና ሊተገበር የሚችል ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ኢትዮጵያ ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ለሰዎች አንገብጋቢ ፈተናዎች የተሻለ ምላሽ ለመስጠት ሁሉን አቀፍ፣ አሳታፊ፣ ፍትሐዊና ወካይ ሊሆን እንደሚገባውም ገልጿል።
የባለብዙ መስክ አሳታፊነት ከተመድ ቻርተር ምሰሶዎች ጋር የተጣጣመ መሆን እንዳለበት ማመላከቱ አይዘነጋም፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version