አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በጋምቤላ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎችና ትምህርት ቤቶች ከ39 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድርጅቱ የጋምቤላ ቅርንጫፍ ተጠሪ ክርስቲን ሐኮንዚ እንዳሉት÷ ከድጋፉ ውስጥ በ12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የተገዙና 20 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ቦርሳ፣ የመማሪያ ደብተርና ሌሎችም ቁሶች ይገኙበታል።
በተለያየ ምክንያት ጉዳት በደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ለጊዜያዊ የመማሪያ ክፍሎች ስራና ለመምህራን አቅም ግንባታ የሚውል በጥሬ ገንዘብ 27 ሚሊየን ብር መበርከቱንም አረጋግጠዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ፓል ካዊች በበኩላቸው÷ዩኒሴፍ በክልሉ ለትምህርት ዘርፍ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ድጋፉ በተለይም በጎርፍና ሌሎች ምክንያቶች ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች በመማር ማስተማር ስራ ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮችን ለማቃለል ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል