Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚና የቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ ጋር ከፍተኛ አመራሮችን በስልጠናና በምርምር አቅማቸውን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ እና የቻይና ብሔራዊ አስተዳደር አካዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጎንግ ዌቢን ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ወደ ስራ ሲገባም ከፍተኛ አመራሮች በስልጠና፣ በምርምር እንዲሁም በማማከር አቅም የሚገነባ ድጋፍ እንደሚገኝ ይጠበቃል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ርዕሰ አካዳሚ ዛዲግ አብርሃ ከተደረጉ ብዙ ውይይቶች በኋላ ዛሬ ለስምምነት መብቃቱን ገልጸዋል።

ስምምነቱ አካዳሚው መሪዎችን ለማብቃት እያከናወነ ያለውን ስራ እንደሚያግዝ ገልጸው፤ ስምምነቱ ከዳር እንዲደርስ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

Exit mobile version