አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር ተተኳሽ መሳሪያዎችን ለመግዛትና የጦር መሳሪያዎችን ለማምረት 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የሀገሪቱ ኮንግረስ እንዲያጸድቅለት ጠየቀ፡፡
አሜሪካ የተለያዩ ጦር መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን እና አሁን ደግሞ ለእስራኤል እየላከች መሆኑ መረጃው አንስቷል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም በሀገሪቱ የጦር መሳሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ የሀገሪቱ ኮንግረስ የጦር መሳሪያዎቹን ለመግዛትና በራስ ለማምረት ገንዘቡን እንዲያጸድቅለት ነው ኮንግረሱን የጠየቀው፡፡
አሜሪካ እና አጋሮቿ ከ600 ቀናት በፊት በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል እየተደረገ በሚገኘው ጦርነት ከ2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ 155 ሚ.ሜ ተተኳሽ መሳሪያዎችን ወደዩክሬን ልካለችም ተብሏል፡፡
ክብ ቅርጽ ያለው 155ሚ.ሜ ተምዘግዛጊ ተተኳሽ መሳሪያ 2 ጫማ (60 ሴንቲሜትር) ርዝመት ያለውና ወደ 45 ኪሎ ግራም የሚመዝን እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የሠራዊቱ ዋና የጦር መሳሪያ ገዥ ዳግ ቡሽ እንዳሉት፥ በአሁኑ ጊዜ በኮንግረሱ እየታየ ያለው የ106 ቢሊየን ዶላር ጥያቄ በቴክሳስ፣ በቴነሲ፣ በቨርጂኒያና በካሊፎርኒያ 155ሚ.ሜ የተተኳሽ መሳሪያ ማምረቻ ተቋማትን ለማዘመን ወይም ለመገንባት ያስችላል።
ገንዘቡ የጦር መሳሪያ ምርት መስመሮችን ያሰፋል የተባለ ሲሆን፥ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ያጠናክራል እንዲሁም አዳዲስ ስራዎችን ይፈጥራል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
ለ155ሚ.ሜ ተተኳሽ መሳሪያን ለመግዛት ከሚበጀተው በጀት ውስጥ ግማሽ ያህሉ የኢንዱስትሪ አቅምን ለማሳደግ ሲውል፥ ቀሪው ደግሞ መሳሪያዎችን ለመግዛት ይውላል ብለዋል ቡሽ።
ለ155 ሚ.ሜ ከሚመደበው ተተኳሽ መሳሪያ ከተመደበው 3 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ውጭም የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የጠየቁት 106 ቢሊየን ዶላር ሌሎች የጦር መሳሪያዎች የበለጠ ለማምረት እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በሩሲና ዩክሬን ጦርነት የ155 ሚ.ሜ ተተኳሽ መሳሪያ ፍላጎት እንደጨመረ ያመላከተው ዘገባው፥ ለኬቭ በሚቀርበው መሳሪያ አጋሮቿ የጦር መሳሪያ እጥረት እየፈተናቸው ነውም ተብሏል፡፡
በ2025 የ155ሚ.ሜ ተተኳሽ መሳሪያዎች ወርሃዊ የምርት ምጣኔን ወደ 100 ሺህ ለማሳደግ መታቀዱም ነው የተነገረው፡፡
ጄኔራል ዳይናሚክስ በቅርቡ ባወጣው የገቢ ሪፖርት፥ 155ሚ.ሜ ተተኳሽ መሳሪያን ጨምሮ ወደ ዩክሬን የተላኩ መሳሪያዎችን ለመተካት ከፔንታጎን ወጪ እንደሚጠቀም ታይምስ ላይቭ ነው የዘገበው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!