Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፍሪካ የፕላስቲክ ቆሻሻ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ከሌላው አካባቢ በተለየ ሁኔታ የፕላስቲክ ቆሻሻ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መጥቷል ሲል በጉዳዩ ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት አመላክቷል፡፡
ቲር ፈንድ እንደተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ገለጻ፤ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት አንድ የእግር ኳስ ሜዳን የሚሸፍን የፕላስቲክ ቆሻሻ በየደቂቃው ይጣላል ወይም ይቃጠላል፡፡
ይህ ልማድ አፋጣኝ መፍትሄ ካልተበጀለት በፈረንጆቹ 2019 ይመረት ከነበረው 18 ቶን ቆሻሻ በስድስት እጥፍ በመጨመር በ2060 የሚመረተው የፕላስቲክ ቆሻሻ መጠን በዓመት 116 ሚሊየን ቶን ይደርሳል ተብሎ እንደሚገመት ተገልጿል፡፡
70 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ከ30 ዓመት በታች በሆነበት ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የፕላስቲክ ፍጆታ መጨመር ዋነኛው ምክንያት የገቢ መጨመር፣ የህዝብ ቁጥር ማደግ፣ የተሽከርካሪ እና ሌሎች ምርቶች ፍላጎት መሆኑ ተጠቁሟል።
በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃም ፕላስቲክን ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት በ2060 ወደ ሶስት እጥፍ ገደማ እንደሚጨምር ይገመታል።
ጉዳዩን አስመልክቶም በቀጣይ ሳምንት በናይሮቢ ኬኒያ ከሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)ጉባኤ በፊት በድርጅቱ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የተደረሰውን ስምምነት ነቅሶ ለማውጣት ተሞክሯል፡፡
በቲር ፈንድ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት ሪች ጎወር “የአካባቢ ውድመት ምልክቶች በዙሪያችን አሉ“ ብለዋል፡፡
ይህ ስምምነትም የፕላስቲክ ቀውስን ለመግታት እና በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ለማሻሻል የሚያስችል አቅም እንዳለው ተናግረዋል።
በናይሮቢ የሚሳተፉ ተደራዳሪዎችም የፕላስቲክ ምርትን ለመቀነስ እና ለማስወገድ በሚያስችሉ የውሉ ማዕከል ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ማሳሰባቸውን ዘ ጋረዲያን ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version