አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ የዘርፉን ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ድርሻ ከፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ሰበታ የሚገኘውን ውዳ ሜታልስ የጎበኙ ሲሆን ከአምራች ኢንዱሰትሪ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
አቶ መላኩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት ÷ መንግስት መሰል አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ የዘርፉን ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ድርሻ ከፍ ለማድረግ ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄን አስጀምሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታትም የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲን በማሻሻል ማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎች እየተዘጋጁ መሆኑን አመላክተዋል፡፡